በ2018 ዓ.ም ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰጠው የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት በክልሉ መንግስት ትምህርት ቢሮ በኩል በይፋ ተገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎ ኤክሴል አካዳሚ በሁለቱም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች በሁለቱም የክፍል ደረጃዎች ያስፈተናቸውን ወንድ 173 እና ሴት 213 በድምሩ 386 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ተከታይ ክፍሎች በከፍተኛ እና አመርቂ በሆነ ውጤት አሳልፏል፡፡
በገንደ ኦዳ ቅርንጫፍ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናውን የተፈተኑ 51 ወንድ እና 59 ሴት በጠቅላላ 110 እንዲሁም የ8ኛ ክፍል የተፈተኑ 23 ወንድ እና 33 ሴት በድምሩ 56 ተማሪዎች በአጠቃላይ 166 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማለፋቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ልዑል አየለ ገልፀዋል፡፡ በገንደ ኦዳ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በክልላዊ ፈተናው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፡-
ከ6ኛ ክፍል
| ደረጃ | የተማሪው/ዋ ሥም | አማካይ ውጤት | ፐርስንታይል ውጤት |
| 1ኛ | ተማሪ ራማ ተስፉ ደሜ | 98.33 | 99.94 |
| 2ኛ | ተማሪ ቢታኒያ እንዳሻው ተፈራ | 97.83 | 99.90 |
| 3ኛ | ተማሪ ሃሌሉያ እሸቱ ፊልታሞ | 97.67 | 99.88 |

ከ8ኛ ክፍል
| ደረጃ | የተማሪው/ዋ ሥም | አማካይ ውጤት | ፐርስንታይል ውጤት |
| 1ኛ | ተማሪ ሄራን ፈይሳ ኢቲቻ | 95.95 | 99.86 |
| 2ኛ | ተማሪ ኢምራን አህመድ ኢብራሂም | 95.24 | 99.77 |
| 3ኛ | ተማሪ የአብፀጋ ታደሰ ከርሲማ | 94.64 | 99.60 |

በተመሳሳይ የኤክሴል አካዳሚ የቢፍቱ ቅርንጫፍ የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናውን የተፈተኑ 57 ወንድ እና 56 ሴት በጠቅላላ 113 ተማሪዎችን እንዲሁም የ8ኛ ክፍል የተፈተኑ 42 ወንድ እና 65 ሴት በድምሩ 107 በጠቅላላው 220 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ቀጣይ ክፍል መሸጋገራቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ቦሰት ቦካን ገልፀዋል፡፡ በቢፍቱ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በክልላዊ ፈተናው የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፡-
ከ6ኛ ክፍል
| ደረጃ | የተማሪው/ዋ ሥም | አማካይ ውጤት | ፐርስንታይል ውጤት |
| 1ኛ | ተማሪ ንፁህ መስፍን አስናቀ | 98.50 | 99.96 |
| 2ኛ | ተማሪ ሩት ሲሳይ ባብሳ | 98.00 | 99.93 |
| 2ኛ | ተማሪ ዮናታን ቢቂላ ደልባ | 98.00 | 99.93 |

ከ8ኛ ክፍል
| ደረጃ | የተማሪው/ዋ ሥም | አማካይ ውጤት | ፐርስንታይል ውጤት |
| 1ኛ | ተማሪ ብሩክ ዘውዴ አየለ | 94.64 | 99.69 |
| 2ኛ | ተማሪ ምህረት አብርሃም ደሳለኝ | 94.05 | 99.59 |
| 3ኛ | ተማሪ ዳግማዊ ደረጀ ተገኝ | 93.33 | 99.45 |

የየቅርንጫፉ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን አቶ ልዑል አየለ እና አቶ ቦሰት ቦካን ለዚህ ከፍተኛ ውጤት አስተዋፅኦ ላደረጉት ለመምህራን፤ ለወላጆች፤ ለአዳማ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት፤ ለክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት፤ ለአካዳሚው ቦርድ እንዲሁም ለኤክሴል ማህበረሰብ በሙሉ ምስጋና በማቅረብ እንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎቹ በቀጣይ ለሚጠብቃቸው የትምህርት ደረጃም ከዚህ የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግቡ ተማሪዎቹ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ እንዲያደርጉ እያሳሰቡ ለተማሪዎቹም ባስመዘገቡት ውጤት እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
2018 E.C. Grade 6 and Grade 8 Regional Examination Results Officially Announced
The results of the 2018 E.C. Grade 6 and Grade 8 Regional Examinations administered by the Oromia Regional State have been officially released by the Oromia Regional Education Bureau.
Following the announcement, Excel Academy proudly achieved a 100% pass rate across both of its campuses and at both grade levels. A total of 386 students—173 boys and 213 girls—sat for the regional examinations, and every student successfully advanced to the next grade with outstanding academic performance.
According to Mr. Leul Ayele, Principal of the Gende Oda Branch, the branch also recorded an exceptional achievement. In the Grade 6 Regional Examination, 110 students (51 boys and 59 girls) sat for the exam and all passed successfully. Likewise, in the Grade 8 Regional Examination, 56 students (23 boys and 33 girls) took the examination, and all achieved passing results.
As a result, all 166 students from the Gende Oda Branch successfully passed the regional examinations and were promoted to the next grade level. The following students from the Gende Oda Branch achieved outstanding results in the Regional Examination:
From Grade Six
| Rank | Name of the Student | Average | Percentile |
| 1st | Rama Tesfa Deme | 98.33 | 99.94 |
| 2nd | Bitaniya Endashaw Tefera | 97.83 | 99.90 |
| 3rd | Haleluya Eshetu Filtamo | 97.67 | 99.88 |

From Grade Eight
| Rank | Name of the Student | Average | Percentile |
| 1st | Heran Feyissa Iticha | 95.95 | 99.86 |
| 2nd | Imran Ahmed Ibrahim | 95.24 | 99.77 |
| 3rd | Yeatsega Tadesse Kersima | 94.64 | 99.60 |

Similarly, Excel Academy’s Biftu Branch also achieved an outstanding 100% pass rate in the 2018 E.C. Regional Examinations.
According to Mr. Boset Bokan, Principal of the Biftu Branch, 113 Grade 6 students (57 boys and 56 girls) sat for the regional examination, and all successfully passed. Likewise, 107 Grade 8 students (42 boys and 65 girls) took the examination, and every student achieved a passing result.
In total, 220 students from the Biftu Branch successfully passed the Regional Examination and were promoted to the next grade level, reflecting the branch’s continued commitment to academic excellence. The following students from the Biftu Branch achieved outstanding results in the Regional Examination:
From Grade 6
| Rank | Name of the Student | Average | Percentile |
| 1st | Netsuh Mesfin Asnake | 98.50 | 99.96 |
| 2nd | Ruth Sisay Babesa | 98.00 | 99.93 |
| 2nd | Yonatan Bikila Deleba | 98.00 | 99.93 |

From Grade 8
| Rank | Student Name | Average | Percentile |
| 1st | Biruk Zewdie Ayele | 94.64 | 99.69 |
| 2nd | Miheret Abreham Dessalegn | 94.05 | 99.59 |
| 3rd | Dagimawi Dereje Tegegn | 93.33 | 99.45 |

The Principals of the two campuses, Mr. Leul Ayele and Mr. Boset Bokan, expressed their sincere appreciation to everyone who contributed to this remarkable achievement. They extended their heartfelt gratitude to the teachers, parents, the Adama City Education Office, the respective Sub-City Education Office, the Excel Academy Board, and the entire Excel Academy community for their invaluable support and commitment. They also congratulated all stakeholders on this outstanding success.
Furthermore, the principals encouraged the students to begin preparing early for the next stage of their academic journey. They emphasized the importance of maintaining their commitment to excellence so that they can achieve even greater success in the coming years.
In closing, they once again congratulated the entire Excel Academy community on this exceptional accomplishment and wished all students continued success in their future academic endeavors.
Congratulations
Excel Academy extends its heartfelt congratulations to all students, teachers, school leaders, and parents for this remarkable achievement. The Academy remains committed to providing high-quality education and nurturing academic excellence, discipline, and responsible citizenship.
Congratulations to all our successful students, and best wishes for even greater achievements in the years ahead.