የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ፤
የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ኤክሴል አካዳሚ ለፈተናው ካስቀመጣቸው 124 (51 ወንድ እና 73 ሴት) ተማሪዎች ውስጥ የ123 ተማሪዎች (51 ወንድ እና 72 ሴት) 99.19% ተማሪዎች ከ50% በላይ በማምጣት የከፍተኛ ትምህርት መከታተል የሚያስችላቸውን ውጤት በማምጣት ማለፍ መቻላቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ደሳለኝ ታደሰ ገልፀዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በመቀጠል ሲያብራሩ አካዳሚው ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ 7 ተማሪዎች (6 ወንድ እና 1 ሴት) ከ500 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን ተማሪ ልዑል ክ/ሚካኤል ገብሬ 566.11/600 በማስመዝገብ የዓመቱን የትምህርት ቤቱን ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ችሏል፡፡ ተማሪ ሰምረዲን ነጋሽ ዳዲ 556.53/600 በማስመዝገብ የሁለተኛውን ደረጃ የያዘ ሲሆን የሶስተኛ ደረጃውን ደግሞ ተማሪ አሴር ፀጋ አደመ 528.39/600 ማስመዝገብ ችሏል፡፡

ሌሎች በአካዳሚው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ ተማሪ መናዬ መብራቱ ደሴ 526.21/600፤ ተማሪ ኢዮሲያስ ኤርሚያስ ወንድሙ 518.53/600፤ ተማሪ ሳሚ ሁሴን አህመድ 512.74/600 እና ተማሪ ፍቅር ተረፈ መንግስቱ 507.27/600 ይገኙበታል፡፡

በመጨረሻ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ደሳለኝ ታደሰ ለዚህ ከፍተኛ እና አመርቂ ውጤት አስተዋፅኦ ላደረጉት በሁሉም ደረጃ ለሚገኙት ለአካዳሚው መምህራን፤ ለወላጆች፤ ለአዳማ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት፤ ለክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት፤ ለአካዳሚው ቦርድ እንዲሁም ለመላው ኤክሴል ማህበረሰብ በሙሉ ምስጋና በመቅረብ እንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልእክትም አያይዘው አቅርበዋል፡፡
2018 E.C. Grade 12 National Examination Results Announced
The results of the 2018 E.C. Ethiopian Secondary School Leaving National Examination have been officially released.
According to the results, Excel Academy had registered 124 students—51 male and 73 female—for the national examination. Of these, 123 students—51 male and 72 female—successfully passed the examination, with 99.19% of the students scoring above 50%, achieving results that qualify them to pursue higher education, according to the school’s Principal, Mr. Desalegn Tadesse.
Explaining the results further, the Principal stated that seven students, six male and one female, scored more than 500 marks out of 600.
Among the top-performing students, Leul K/Michael Gebre achieved the highest score of the year, scoring 566.11 out of 600. Semredin Negash Dadi ranked second with a score of 556.53 out of 600, while Aser Tsega Ademe secured third place with 528.39 out of 600.
The results demonstrate the strong academic performance of Excel Academy’s Grade 12 students in the 2018 E.C. national examination.

Other students who achieved outstanding results at the Academy include Menaye Mebratu Dese, who scored 526.21 out of 600; Eyosias Ermias Wondimu, who scored 518.53 out of 600; Sami Hussein Ahmed, who scored 512.74 out of 600; and Fikir Terefe Mengistu, who scored 507.27 out of 600.

Finally, the school’s Principal, Mr. Desalegn Tadesse, expressed his sincere appreciation to all those who contributed to achieving this outstanding and remarkable result.
He extended his gratitude to the Academy’s teachers at all levels, parents, the Adama City Education Office, the Sub-City Education Office, the Academy’s Board, and the entire Excel community for their valuable contributions and support.
The Principal also conveyed his heartfelt congratulations to the entire Excel community on this remarkable achievement.