የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተጀመረ፤
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የፌድራል ትምህርት ሚኒስቴር እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ባወጡት ዓመታዊ የትምህርት ካለንደር መሰረት በኤክሴል አካዳሚ በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ከዛሬ መስከረም 05/2019 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ተጀምሯል፡፡

በት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲተላለፍ፤
በየቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት መርሀ-ግብር የተከናወነ ሲሆን ተማሪዎቹን እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ አካዳሚያችን እና ወደ የመትወዱት ትምህርት ቤታችሁ በሰላም መጣችሁ በማለት ትምህርት መጀመሩን የሚያበስር የችቦ ማብራት ስነ-ስርዓት ተከናውናል፡፡

ትምህርት መጀመሩን አስመልክቶ በተማሪዎች የችቦ ማብራት መርሀ-ግብር ሲከናወን፤
በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ ርዕሰነ መምህራን ለየትምህርት ቤቱ አዲስ ተማሪዎች ከነባሮቹ ጋር የማስተዋወቅ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ በተማሪዎች ሊጠበቁ የሚገባቸው የስነ-ስርዓት አካሂዶች ላይ አጠር ያለ ገለፃ ከተከናወነ በኃላ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተማሪዎች በየተመደቡበት ክፍል በመግባት ተከናውናል፡፡

በመጀመሪያው የትምህርት ቀን የመማር ማስተማር ሂደቱ በክፍል ውስጥ ሲከናወን፤
The 2026/27 Academic Year Has Officially Begun
The 2026/27 academic year has officially commenced at Excel Academy in all of its branch schools starting today, September 15, 2026 E.C., in accordance with the annual academic calendar issued by the Federal Ministry of Education and the Regional Education Bureau.

School Principals Delivering Welcome Messages to Students
Opening ceremonies were conducted at each branch school to mark the beginning of the new school year. During the events, students were warmly welcomed back to their beloved schools and to the Academy for the 2019 academic year. As part of the celebration, a torch-lighting ceremony symbolizing the official start of the school year was held.

Students Participating in a Torch-Lighting Ceremony Marking the Start of the Academic Year
At the branch schools, principals introduced newly enrolled students to returning students and provided brief orientations on school rules, discipline, and expected codes of conduct. Following these introductory sessions, the regular teaching and learning process officially began, with students proceeding to their assigned classrooms to start their studies.

Nursery Students Celebrating Their First Day of School
Excel Academy wishes all students a successful and productive 2026/27 academic year.